የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መግለጫ

ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ባቀረባቸው ዘገባዎች በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ያልተመጣጠነ ኃይል በመጠቀም የመንግሥት አካላትን ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሶማሌ እና በኦሮምያ ክልል በደረሰ ግጭት የዜጎች ህገ መንግሥታዊ መብቶች መጣሳቸውን  ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ 3 ወራት በፊት በላከው ዘገባ ማሳወቁን ገለፀ። የከሚሽኑ ሃላፊ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሥሪያ ቤታቸው ከዚህ ቀደም ባቀረባቸው ዘገባዎችም በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ያልተመጣጠነ ኃይል በመጠቀም የመንግሥት አካላትን ተጠያቂ ማድረጉን አስታውሰዋል። ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ በየአካባቢው ስለሚፈናቀሉ ሰዎች እና ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *