ሃዊ በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች! – የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽ/ቤት ቤይሩት

ሃዊ ጉደታ ሂርጳ የተባለች ዜጋችን በትናንትናው ዕለት በአሰሪዎቿ ተደብድባ አደጋ እንደደረሰባት ይታወቃል።

ሆኖም ሃዊ ላይ የደረሰውን አደጋ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች እተሰራጨ ይገኛል ።

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ቆንስላ ጽ/ቤቱ የአደጋ አድራሾችን አሳፋሪ ድርጊት በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን እየገለፀ ጉዳዩን በተመለከተ ከፖሊስ ፣

ካሪታስ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሊባኖስ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን ክትትል እያደረገ መሆኑን እንገልፃለን።

ሃዊ በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ፣ ከቤተሰቦቿ ጋር በስልክ የተገናኘች መሆኗን

በካሪታስ መጠለያ እንደምትገኝ እያሳወቅን በቆንስላው አማካይነት ጉዳዩ ክትትል ተደርጎበት ሲያልቅ መረጃ የምናደርስ መሆናችንን እንገልፃለን።

የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽ/ቤት
ቤይሩት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *